January 7, 2025

ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

ህገ መንግሰታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። በሲዳማ ዞን በሚገኙ 36 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድሮች የተውጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን በህገ መንግስቱ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ ነው ተብሏል።

Sidama Grand Rally

ህገ መንግሰታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። በሲዳማ ዞን በሚገኙ 36 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድሮች የተውጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን በህገ መንግስቱ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ ነው ተብሏል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫውቻ፣ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ እና የወጣቶች ተወካይ ንግግር አድርገዋል። የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫውቻ፥ የሲዳማ ህዝብ በክልል ተዋቅሮ ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ማቅረብ ከጀመረ ረጅም ዓመታትን ማስቆጠሩን ተናግረዋል። በመሆኑም የሲዳማ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት ምላሽ መሰጠት እንዳለበትም አቶ ቃሬ ጫውቻ ገልፀዋል። የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ በበኩላቸው በዛሬው እለት የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በህገ መንግስቱ መሰረት ክልል የመሆን ጥያቄን ለማቅረብ የተካሄደ ነው ብለዋል። የሲዳማ ህዝብ ክልል ለመሆን እያቀረበ ያለው ጥያቄው በህገ መንገስቱ መሰረት በአፋጣኝ መልስ ማግኘት ያለበት ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል። የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች “ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር! የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው! የሪፈረንደም ቀን ይወሰን !” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል። ጥዋት ላይ መነሻውን ከሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻውን ሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲዮም ላይ በማድረግ ነው ፍፃሜውን ያደረገው። የደቡብ ክልል ምክር ቤት በጥቅምት ወር ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን ተከትሎ እንዲፈጸም ባለፈው ጥቅምት ወር ባካሄደው ጉባኤ መወሰኑ ይታወሳል። በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት ክልል የመሆን ጥያቄ የሚያቀርበው ብሄር፣ ብሄረሰብ ወይም ህዝብ በብሄር ብሄረሰብ ወይም ህዝብ ምክር ቤት በሁለት ሶስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘት ያለበት ሲሆን፥ የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ይህንን ክልል የመሆን ጥያቄን ባለፈው ዓመት ተቀብሎ ማፅደቁ የሚታወስ ነው። ጥያቄው ለክልሉ ምክር ቤት ባለፈው ጥቅምት ወር የቀረበ ሲሆን፥ ቀጣይ ሂደት በተመለከተ የክልሉ ምክር ቤት ህዝበ ውሳኔ በጠየቂው ዞን የሚካሄድበትን ጊዜ እና ሁኔታን እንደሚወስን ምክር ቤቱ አስታውቆም ነበር።

About Post Author