January 7, 2025

የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ሰብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ሰብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን የፓርቲው ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዩሃንስ ቧያሌው ገለፁ። ሀላፊው ማዕከላዊ ኮሚቴው ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ባካሄደው ውይይት የተመለከታቸውን አጀንዳዎች እና ያስቀመጣቸውን የውሳኔ ሀሳቦች አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

Yohanes-Buayalew

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ሰብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን የፓርቲው ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዩሃንስ ቧያሌው ገለፁ።

 
ሀላፊው ማዕከላዊ ኮሚቴው ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ባካሄደው ውይይት የተመለከታቸውን አጀንዳዎች እና ያስቀመጣቸውን የውሳኔ ሀሳቦች አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በመግለጫቸው ላይ እንዳመለከቱትም ኮሚቴው በስብሰባው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎችን ገምግማል።
 
ይህንንም መሰረት በማድረግ በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ዙሪያ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን ነው ያመለከቱት።
 
በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የፀጥታ ችግሮች እንደነበሩ በመመልከትም አሁን ላይ መሻሻሎች መኖራቸውን ገምግሟል።
 
ኮሚቴው አመራሩን ለማጠናከር የሚያስችሉ ሁኔታዎችንም በመገምገምም የፓርቲውን የተወሰነ አመራር በአዲስ የመተካት ስራ ማከናወኑም ተገልጿል።
 
የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶክተር አምባቸው መኮንንን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።

About Post Author