January 4, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን

5FD15EB4-2292-4E33-B991-D900AEBC4997

የብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መስተዳድሮችን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር 7/1984 መሠረት አዲስ አበባ) ክልል14 በመባል እራሱን ሲያስተዳደር ነበር፡፡

የኢፌዲሪ ሕ/መ አንቀጽ 49(5) የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅም የተጠበቀ ነዉ፡፡

ቀደም ሲል ከሕገ/መንስቱ በፊት አ.አ. የሚትባል ወሰኗ የሚታወቅ ከተማ እንደነበረች ከሕገ መንግስቱ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡ ከሕገ መንግስቱ በኋላም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በሚመለከት የተለያዩ ሕጎች ወጥቷል፡፡እነዚህም ሕጎች ፡-የመጀመሪያዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 87/1989 ሲሆን አንቀፅ 2(1) ሥር ለአ.አ. በተሰጠዉ ትርጉም መሠረት አ.አ. ማለት የከተማዉ ክልልና 25 የገጠር ቀበሌዎች የሚያጠቃልል ቦታ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

ይህ ወሰን ሕገ መንግስቱ ከሚያዉቀዉ ወሰን ሁለት እጥፍ ነዉ፡፡ በተሻሻለው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 311/1995፣ላይ ይህ ለአ.አ. በተሰጠዉ ትርጉም አልተሸሻለም፡፡ የተሻሻለው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995፣ አንቀፅ 5 ሥር ቀደም ሲል ያለዉ ወሰን እንደለ ሆኖ የከተማዉ ወሰን አስተዳደሩ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚያደርገዉ ስምምነት ወይም በፌዴራል መንግስት ይወሰናል ይላል፡፡

ይህ አዋጅ ቀደም ሲል የተወሰነዉን ወሰን እንዳለ ሆኖ ወደፊት ሌሎች ቦታዎችን የመጨመር ፍላጎት እንዳለዉ እና አ.አ. እየሰፋች እንደምትሄድ ያለዉን ፍላጎት ያሳያል፡፡ የአ.አ. ወሰን እንደነገሩ ሁኔታ ከኦሮሚያ ጋር በመነጋገር ወይም በፌዴራል መንግስት ወደፊት ሊወሰን እንደሚችል ያሳያል፡፡ በመሆኑም በሕገመንግስቱ ብቻ ነዉ እንጂ በዚህ አዋጅ መሠረት የአ.አ. ወሰን እስከ አሁን እንደማይታወቅ ነዉ፡፡ የተሻሻለው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 408/1996. ቀደም ሲል ስለ አ.አ. ወሰን በአዋጅ ቁጥር 361/1995 የተጠቀሰዉ አልተሸሻለም፡፡

አዋጁም መሠረት የአ.አ. ወሰን ከዚህ በፊት የተወሰነ ቢሆንም እንዳልተወሰነ ተቆጥሮ በአዲስ ወሰን ከአሁኑ ሰፋ የሚትል አዲስ አ.አ. ወደፊት የምትወለድ እንደሆነ ያሳያል፡፡ አ.አ. ከተማ የከዚህ በፊቱ ወሰኗ መሠረት በማድረግ ሳይሆን አሁን ባለችበት ሁኔታ ወይም ተጨማሪ ቦታዎችን በማከል ወሰን ሊበጅላት እንደሚገባ መፈለጉን ያመለክታል፡፡ ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅም እንድታሟላ የምትጠበቀዉ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ጋር ያላት ወሰን በ1984 በዉል ተለይቶ የሚታወቅ ነዉ፡፡ በመሆኑም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቅርብ ቀን የወሰን ምልክትም እንደሚያደርግ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

By Abduljebar Hussien.

About Post Author