November 21, 2024

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትና ፔትሮ ቻይና የአንድ ዓመት የነዳጅ አቅርቦት ስምምነት ፈረሙ

ፔትሮ ቻይና የነዳጅ አቅርቦቱን በየዕለቱ በሚውለው የዓለም የነዳጅ አማካይ ዋጋ ላይ ተመሥርቶ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ነዳጁን ወደብ ድረስ በማጓጓዝ ያሸነፈበት ፕሪምየም ዋጋ፣ ለአውሮፕላን ነዳጅ 5.7 ዶላር በበርሜል፣ ለናፍጣ 4.78 ዶላር በርሜል፣ ለቤንዚን 5.7 ዶላር በበርሜል ነው፡፡

በፔትሮ ቻይናና በነዳጅ አቅራቢ ድርጅት መካከል የግዥ ስምምነቱ ረቡዕ፣ ታኅሳስ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. በተከናወነበት ወቅት እንደተገለጸው፣ እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 1 ቀን 2019 እስከ ዲሴምበር 31 ቀን 2019 ድረስ ለአንድ ዓመት የሚውለውን የነዳጅ ፍጆታ ፔትሮ ቻይና በዓለም ዋጋ መሠረት የወርኃዊ አማካዩን  በማስላት ያቀርባል፡፡ ለፔትሮ ቻይና የአገልግሎት ክፍያ የሚፈጸመውም ከየአንዳንዱ በርሜል ላይ በሚሰላ ፕሪሚየም ዋጋ መሠረት ይሆናል፡፡

ፔትሮ ቻይና የነዳጅ አቅርቦቱን በየዕለቱ በሚውለው የዓለም የነዳጅ አማካይ ዋጋ ላይ ተመሥርቶ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ነዳጁን ወደብ ድረስ በማጓጓዝ ያሸነፈበት ፕሪምየም ዋጋ፣ ለአውሮፕላን ነዳጅ 5.7 ዶላር በበርሜል፣ ለናፍጣ 4.78 ዶላር በርሜል፣ ለቤንዚን 5.7 ዶላር በበርሜል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ከአሸናፊው ኩባንያ ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት፣ ለአንድ ዓመት 1.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ናፍጣ፣ 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ቤንዚንና 240 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅ ያቀርባል፡፡ ባለፈው ረቡዕ የተደረገውን ነዳጅ የማቅረብ ስምምነት የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅትን በመወከል አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ሲፈርሙ፣ በፔትሮ ቻይና በኩል ደግሞ የኩባንያው ተወካይ ሚኒስትር ደንግ ፈርመዋል፡፡

About Post Author