January 4, 2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱን “የአፍሪካ ሻምፒዮን ሽልማትን” ማግኘቱ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱን “የአፍሪካ ሻምፒዮን ሽልማትን” ማግኘቱ ተገለፀ፡፡ አየር መንገዱ በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፎረም ላይ ነው የዓመቱ “የአፍሪካ ሻምፒዮን ሽልማት” የተበረከተለት።

ETH-AIR-CEO

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓመቱን “የአፍሪካ ሻምፒዮን ሽልማትን” ማግኘቱ ተገለፀ፡፡ አየር መንገዱ በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፎረም ላይ ነው የዓመቱ “የአፍሪካ ሻምፒዮን ሽልማት” የተበረከተለት።

የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፎረም በትናንትናው ዕለት በሩዋንዳ ኪጋሊ የተጀመረ ሲሆን፥ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካና የዓለም ሀገራት ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ፎረሙ በአፍሪካውያን የእርስ በርስ ግብይት፣ ኢንቨስትመንት፣ በአህጉሪቱ ኢኮኖሚ ውህደት እንዲሁም የግል ሴክተሩን ማጎልበት፣ ምቹ ፖሊሲዎችን መቅረጽና ዘላቂና የተረጋጋ ንግድ ላይ ትኩረት በማድረግ እየተካሄደ ነው።

About Post Author