November 21, 2024

የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ

ኢትዮጵያ ከራሷ ዜጎች በዘለለ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የምትበቃ በመሆኗ ይህንን ከግምት ማስገባት መልካም ነው ሲሉም ገልፀዋል። የኦዲፒ አላማ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በእኩል ድምጽ በነጻነት የሚኖሩባትን ሀገር መፍጠር ነው፤ በዚህ ረገድም ከሁሉም ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል:: ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክትም መለያየትን የሚሰብኩ አስተያየቶችን ወደ ጎን በመተው በጋራ መቆም አለብን ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) 29ኛ የምስረታ በዓል እና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኦዲፒ ሊቀ መንበርና የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ የኦዲፒን የምስረታ በዓል ስናከብር ለአዳዲስ ድል እና ገድል እየተዘጋጀን መሆን አለበት ብለዋል።

ኦዲፒ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚኮሩባት፣ የሚሰራበት እና የማይሸማቀቁትት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራልም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም፥ ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ሀሳቦች አዲስ አበባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምት ሂዶ እንደሚሰራውና የኔ ናቸው እንደሚለው ሁሉ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ነች፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከራሷ ዜጎች በዘለለ ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የምትበቃ በመሆኗ ይህንን ከግምት ማስገባት መልካም ነው ሲሉም ገልፀዋል። የኦዲፒ አላማ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በእኩል ድምጽ በነጻነት የሚኖሩባትን ሀገር መፍጠር ነው፤ በዚህ ረገድም ከሁሉም ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ነው ብለዋል:: ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክትም መለያየትን የሚሰብኩ አስተያየቶችን ወደ ጎን በመተው በጋራ መቆም አለብን ሲሉም ተናግረዋል።

ለኦዲፒ አባላት ባስተላለፉት መልክት ደግሞ፥ ኦዲፒ በማንኛውም ሁኔታ ድምፆች መታፈን የለባቸውም የሚለውን አላማ ይዞ መነሳቱ መዘንጋት እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል። ማንኛውም ሀሳብ የሚንሸራሸርበት ኢትዮጵያን መፍጠር የትግላችን ውጤት መሆኑንም መገንዘብ አለብን ሲሉም ተናግረዋል።

አሁን ካለንበት የለውጥ ሂደት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስደንጋጭ ሀሳቦችን ልትሰሙ ትችላላችሁ፤ እነዚህን ከመደናገጥ ይልቅ የተሻለውን ሀሳብ በመውሰድ ሌላውን ወደጎን መጣል አለብን ብለዋል። አሁን የጀመርነውን ድል ማንም ወደ ኋላ አይመልሰውም ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

እህት ድርጅቶችም በተጠናከረ እና በወንድማመችነት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ እናሸጋግር ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በዚህ በዓል ላይ የተገኙት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሊቀመንበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው  ለውጥ ሁሉ ፈተና እንዳለው ገልጸው ፈተናውን በጋራ በመሰለፍ መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ለመስራት ሁሉም መነሳት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

About Post Author