January 1, 2025

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

President

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ዴቪድ ቢዝሊ ጋር ተወያይተዋል፡፡በውይይታቸውም ድርጅቱ በኢትዮጵያ እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እና ለወደፊትም ሊሰራቸው ባሰባቸው እቅዶች ዙሪያ መክረዋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በተለያዩ የአስቸኳይ ምግብ አቅርቦት እና በምግብ እህል ራስን በሚያስችሉ መርሃ ግብሮች ላይ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ድርጅቱ ለ1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች የኢትዮጵያ መንግስት በሴፍቲኔት ፕሮግራም በኩል የሚያቀርበውን ድጋፍ እያገዘ ነው።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ከሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች ውስጥ 700 ሺህ ለሚሆኑት የምግብ አቅርቦት ለማሟላት በመደገፍ ላይ ይገኛል።በተያያዘም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአውስትራሊያው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ዱተን ጋር ተወያይተዋል።በውይይታቸውም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና በተለያዩ የትብብር ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል።

About Post Author