January 9, 2025

29 ቢሊየን ብር በሚገመት ወጪ የሚከናወነው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የፕሮጀክቱን በይፋ መጀመር ያበሰሩ ሲሆን፥ ፕሮጀክቱ የሁሉም ኢትዮጵያውያን እና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት አዲስ አበባ ከተማ እንደ ስሟ የምትኖር ከተማ ለማድረግ የሚካሄድ መሆኑንም ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል።

Addis-Abab-river-bank-project-750x430 (1)

የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን የማስጀመር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። የወንዝ ዳርቻ የአረንጓዴ መናፈሻ የመጀመርያ ፕሮጀክት አካል የሆነው “የቤተ መንግስት አካባቢ የከተማ መናፈሻ” ስራው ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

የፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የፕሮጀክቱን በይፋ መጀመር ያበሰሩ ሲሆን፥ ፕሮጀክቱ የሁሉም ኢትዮጵያውያን እና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት አዲስ አበባ ከተማ እንደ ስሟ የምትኖር ከተማ ለማድረግ የሚካሄድ መሆኑንም ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል። የሀገር እድገት እና ውበት አንዱ መለኪያ የከተማ ውበት እና ፅዳት ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፥ ምክንያቱ ደግሞ ከተማ የሁሉም ነገር ማእከል ስለሆነ ብለዋል። አዲስ አበባን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሪነት፤ በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪነት እና በከተማዋ ነዋሪዎቿ ጋር በመሆን በጋራ ድንቅ ከተማ መገንባታቸነን እንቀጥላለን። በዛሬው እለት የተጀመረው እና በቫርሜሮ ኩባንያ የሚካሄደው ከተማዋን ወደ አንድ ከፍታ የሚያሻግር ፕሮጀክት የሁላችንም አሻራ የሚያርፍበት የጋራ ፕሮጀክታችን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በዛሬው እለት እንደ ማሳያ የሚጀመረው ከእንጦጠ እስከ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ያለው የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምእራፍ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ይፈጃል ያሉ ሲሆን፥ ወጪውም በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ነው ብለዋል። ፕሮጀክቱ የሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ነው ያሉት ምክት ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ለፕሮጀክቱ እውን መሆን እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል። ለፕሮጀክቱ እውን መሆን ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ከፍተኛ አስተዋፅሶ ላደረጉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በራሳቸው እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአዲስ አበባ የባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፥ አዲስ አበባ ከተማ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን እና ባህላዊ እሴቶችን በውስጧ የያዘች ውብ ከተማ ነች ብለዋል። ሆኖም እን እንደ ስሟ ሰፋ ያሉ የመዝናኛ እና የመናፈሻ ስፍራዎች የላትም ያሉ ሲሆን፥ ዛሬ በይፋ የተጀመረው ፕሮጀክት ግን ከተማዋን ከውበትን አልፎ የቱሪዝም መዳረሻ የሚያደርጋት ነው ሲሉም ተናግረዋል። የቫርሜሩ ኩባንያ ተወካይ በበኩላቸው የተሰጠን ሀላፊነት በጣም ከባድ ነው ያሉ ሲሆን፥ ሌት ተቀን በመስራት ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ እውን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። በ29 ቢሊየን ብር ወጪ የሚከናወነው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት በ3 ዓመታት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት አዲስ አበባ ከተማን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረ ሆኖ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው። ፕሮጀክቱ በ3 ዓመታት ውስጥ 4 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ድልድዮች፣ ሰው ሰራሽ ሐይቆች፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የመዝናኛ ማዕከላት፣ የውኃ ትራንስፖርት እና የንግድ ማዕከላትን ያካተተ ግንባታ እንደሚካሄድም ታውቋል። ፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ ከተማን የአረንጓዴ ሽፋን ከ0 ነጥብ 3 ወደ 7 በመቶ ከፍ የሚያደርግ መሆኑም ተነግሯል።

About Post Author