January 6, 2025

የፌዴራል ስርዓት ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም- ኦዲፒ (ODO)

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ለመመለስ እንደሚሰራ በመግለጽ፥ የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይም እየተሰራበት ያለ መሆኑን ገልጿል። ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ላይም ትኩረት በመስጠት እየሰራበት መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል።

ODP

ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።

ለፌደራል ስርዓቱ መምጣት ከፍተኛ ዋጋ ተከፍሎበታል ያለው ፓርቲው፥ ስርዓቱ ለድርድር የማይቀርብ መሆኑንም አስታውቋል በመግለጫው። በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑንም ኦዲፒ በመግለጫው አስታውቋል። በአሁኑ ወቅትም በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የፌዴራል ስርዓቱን ሊያፈርስ እንደሆነ እንዲሁም ህብረተሰቡ በፌዴራል ስርዓት ላይ ያለውን እምነት እና ተስፋ እንዲቀንስ ከፍተኛ የሆነ የሀሰት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑንም ገልጿል። የሀሰት ዘመቻው ሁለት ዓላማ ያለው ነው ያለው ኦዲፒ፥ ከእነዚህም አንደኛው የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሁን ያለውን ለውጥ በጥርጣሬ እንደሚመለከቱ ማድረግ ነው ብሏል። በዚህም የራሳቸውን ባህል፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ታሪክ ማሳደግን በትግል እና በመስዋእትነት ያገኙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የፌደራል ስርዓቱ ሊፈርስ ነው በሚል በጥርጣሬ ተቃውሞ እንዲያስነሱ ታስቦ የሚደረግ ሴራ መሆኑንም ገልጿል። በተጨማሪም የኦሮሞን ህዝብ “ተጨማሪ መብት ማግኘትህ ቀርቶ ከዚህ ቀደም የተገኘውን መብት ልታጣ ነው” በሚል በማደናበር እርስ በርስ ለማጋጨት ያለመ መሆኑንም አስታውቋል። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ለመመለስ እንደሚሰራ በመግለጽ፥ የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይም እየተሰራበት ያለ መሆኑን ገልጿል። ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ላይም ትኩረት በመስጠት እየሰራበት መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል። ኦዲፒ ለተጨማሪ ድል ይሰራል እንጂ ከዚህ ቀደም የተገኙ ድሎችን አያከሽፍም ያለው ፓርቲው፥ በፌደራል ስርዓት ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥም ገልጿል።

About Post Author

1 thought on “የፌዴራል ስርዓት ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም- ኦዲፒ (ODO)

Comments are closed.