ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ

የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 3 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቂሊንጦ ማረፊያ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት ከኃላፊዎች በተሰጠው ትዕዛዝ ማንነታቸው ባልተለየ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት በተተኮሰ ጥይት በታራሚዎች ላይ ከባድ አካላዊ ጉዳት እና ህይወታቸው እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡

ተከሳሾች በቅደም ተከተላቸው መሰረት ኦፊሰር ገብረማርያም ወልዳይ አብርሃ፣ ሱ/ኢን/ት አስገለ ወልደ ጊዮርጊስ ወ/ማርያም፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት አሰፋ ኪዳኔ ተድላ፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት ገ/እግዚአብሄር ገብረ ሃዋርያት፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት ተክላይ ሀይሉ ተክለ ሃይማኖት፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት አቡ ግርማ ወ/ሚካኤል፣ ዋ/ሱ/ኢን/ት አዳነ ሀጎስ ህሻ እና ዋ/ሱ/ኢን/ት ገብራት መኮንን ገብሩ ናቸው፡፡

ተከሳሾች በፌደራል ማረሚያ ቤቶች የቂሊንጦ፣ የዝዋይ እና የሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡ የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 3 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቂሊንጦ ማረፊያ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት ከኃላፊዎች በተሰጠው ትዕዛዝ ማንነታቸው ባልተለየ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት በተተኮሰ ጥይት በታራሚዎች ላይ ከባድ አካላዊ ጉዳት እና ህይወታቸው እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡

በተፈጠረው የማረሚያ ቤት ቃጠሎ ምክንያት ከ400 በላይ የሚሆኑ በእስር ላይ የነበሩ ታራሚዎችን ወደ ሸዋሮቢት ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት እንዲወሰዱ በማድረግ የነበራቸውን ንብረት በመቀበል በባዶ እግራቸው በቁምጣ ብቻ በመኪና ላይ እንዲጫኑ በማድረግ፤ ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ሲደርሱም በመስመር በማሰለፍና በማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት በዱላ በመደብደብ፣ 175 የሚሆኑ ታራሚዎችን ደግሞ ባዶ ቤት የሴሚንቶ ወለል ላይ እንዲተኙ በማድረግ፣ ለሁለት ለሁለት በካቴና በማሰር ለረዥም ጊዜ በማቆየት፤ በካቴና እጃቸውን ሁለት ሁለት እያደረጉ በማሰር በባዶ እግራቸው መፀዳጃ ቤት እንዲጠቀሙ በማድረግ፣ እጃቸውን ሳይታጠቡ ምግብ እንዲመገቡ እና ህክምና በመከልከል እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ አድርገዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ምርመራ ጨርሰው ወደ ሌላ ክፍል ሲዘዋወሩ ለ42 ቀናት ከአልጋ ጋር ለ24 ሰዓት በካቴና በማሰር፣ 37 የሚሆኑ ተበዳዮች ፍርድ ቤት ረበሻችሁ በማለት ከ3 እስከ 6 ወር እጃቸውን በካቴና አስሮ ጨለማ ቤት ውስጥ በማሰር፣ ግለሰቦች የለበሱትን ልብስ በማስወለቅ ቲሸርትና ቁምጣ በማስለበስ እና በፌሮ ብረት እንዲደበደቡ በማድረግ ኢ- ሰብአዊ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ያደረጉ በመሆኑ በፈጸሙት ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የተከሳሽ ጠበቆች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የተከራከሩ ቢሆንም የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡

ተከሳሶችም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ዐቃቤ ህግ የመሰረተባቸው ክስ በችሎቱ ተነቦ ለቀረበባቸው ክስ መልስ ይዘው ለመቅረብ ለየካቲት 27/20011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

About Post Author